ኢትዮጵያውያን የጥፋት አላማ የሚያራምዱ አካላትን እድል ሳይሰጡ ማክሸፍ ይኖርባቸዋል -አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያውያን የጥፋት አላማ የሚያራምዱ አካላትን እድል ሳይሰጡ ማክሸፍ ይኖርባቸዋል -አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ
አዲስ አበባ ህዳር 29/2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጥፋት አላማ የሚያራምዱ አካላትን እድል ሳይሰጡ ማክሸፍ እንደሚኖርባቸው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ አስታወቁ።
15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የአገር አቀፍ ሲምፖ ዚየም መርሐግብር በስካይ ላይት ሆቴል በመካሔድ ላይ ይገኛል።
በመርሐግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ የሕግ የበላይነትን ማስከበር ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስቀጠልና ሕብረ ብሔራዊነት አንድነትን ለማስጓዝ ቀዳሚ ተግባር ነው ብለዋል።
በዚህም ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመጣልና የህዝቦችን አንድነት ለማፍረስ በተንቀሳቀሰው የህወሓት ሀይል ላይ የህግ ማስከበር እርምጃ ተወስዷል በማለት ገልጸዋል።
የጥፋት ቡድኑን ለማስወገድ መስዋዕትነት ለከፈሉ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
ዋጋ የተከፈለለትን የህዝቦች አንድነት ለማስቀጠል የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጥፋት አላማ የሚያራምዱ አካላትን እድል ሳይሰጡ ማክሸፍ ይኖርባቸዋል ሲሉም ነው አፈ ጉባኤው የገለጹት።
ፍትሐዊ ተጠቃሚነትትን ለማረጋገጥ ከሚያለያዮ ሐሳቦች በመራቅ በጋራ እሴቶች ላይ መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል።