የዘንድሮውን የብሄር ብሬረሰቦች ቀን ስናከብር ሀገራዊ አንድነትን በሚጠናክር መሆን አለበት- ዶክተር ሂሩት ካሣው - ኢዜአ አማርኛ
የዘንድሮውን የብሄር ብሬረሰቦች ቀን ስናከብር ሀገራዊ አንድነትን በሚጠናክር መሆን አለበት- ዶክተር ሂሩት ካሣው
አዲስ አበባ ህዳር 28/2013 (ኢዜአ) የዘንድሮውን የብሄር ብሬረሰቦች ቀን ስናከብር ሀገራዊ አንድነትን በሚጠናክር መልኩ መሆን አለበት ሲሉ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሣው ተናገሩ።
15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
በመርሃ ግበሩ ላይ የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሣው ባደረጉት ንግግር እለቱን ስናከብር ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ መሆን አለበት ብለዋል።
ከዚህ ቀደም እለቱ ሲከበር ከሀገራዊ አንደነት ይልቅ በብዛት ብሄርተኝነት ላይ በማተኮር ነበር ብለዋል።
በመሆኑም የዘንድሮውን በዓል ስናከብር ከጎጠኝነት አስተሳሰቦች በመላቀቅ ለህብረ ብሄራዊነትና አገራዊ አንድነታችን ትኩረት በመስጠት መሆን አለበት ብለዋል።
በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሐብታሙ ሲሳይ በበኩላቸው እለቱን ስናከብር ከፋፋዮችንና ሴረኞችን በጋራ ታግለን መጣልንበት ማግስት ነው ብለዋል።
ኅብረተሰቡ አሁን ላይ ያለውን መነቃቃት በመጠቀም የጎጠኝነትና ከፋፋይ እሳቤዎችን በመታገል መሆን ይኖርበታል ነው ያሉት።
15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን “እኩልነትና ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ሃሳብ በመከበር ላይ ይገኛል።