ቀጥታ፡

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለተሳተፉ ወጣቶችና ተቋማት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ ህዳር 28/2013 በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ወጣቶችና የተለያዩ ተቋማት እውቅና ተሰጣቸው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ የበጎ ፈቃድ ተግባር  የእለት ተእለት ስራ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።

በ2012 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎ ተሳትፈው አስተዋፆ ላደረጉ ወጣቶችና ተቋማት እውቅና መሰጠቱም ለቀጣይ ስራ የሚያነሳሳ መሆኑን ተናግረዋል።

በሚኒስቴሩ የወጣት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ህይወት ሀይሉ በበኩላቸው ወጣቶች በተለያዩ የአገልገሎት ዘረፎች በመሳተፍ ባደረጉት አስተዋፆ አመስግነዋል።

በዚህም የተሰጣቸው እውቅና የሚገባቸውና ለቀጣይ ስራ የሚያነሳሳቸው መሆኑን ተናግረዋል።

"በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ሃሳብ ለተከናወነው የበጎ አገልገሎት እውቅና መሰጠቱ አገልግሎቱ በቀጣይ እንዲጠናከር ሰፊ እድል ይፈጥራልም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ወጣት ታረቀኝ አብዱልጀባር በበኩሉ ወጣቱ ከመንግስትና ህዝብ ጎን በመቆም በቀጣይም የተለያዩ ተግባራትን ለማገዝ ዝግጁ ነው ብሏል።

በዕለቱ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የራሳቸውን አስተዋፅኦ ላበረከቱ የክልል ወጣት ፌዴሬሽኖችና ለተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ሌሎች ተሳታፊ አካላት የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ 

የዘንድሮው የአለም የበጎ ፈቃደኞች ቀን ፟በአንድነት በበጎ ፈቃደኝነት ሁለን ማድረግ እንችላለለን፟ በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም