ቀጥታ፡

በሰሜን ኢትዮጵያ በተደረገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ኢትዮጵያዊነት አሸንፏል - የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27/2013 (ኢዜአ) በሕወሓት ጁንታ ላይ በተወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ኢትዮጵያዊነት አሸንፎ የወጣበት መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

የህግ ማስከበር ዘመቻው ተጠናቆ ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ስራ ምእራፍ ላይ መደረሱ ይታወቃል።

የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ያካሄደው ስብሰባ መጠናቀቁን አስመልክቶ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም በሰጡት መግለጫ “ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አገሪቷን ወቅታዊ ሁኔታ፣ አገራዊና አለም አቀፋዊ የፖለቲካ አሰላለፎች እንዲሁም በዝግጅት ላይ የሚገኘውን የፓርቲውን 'ማኒፌስቶ' አስመልክቶ ውይይት አድርጓል” ብለዋል።

በዚህም መሰረት የሕወሓት ጁንታ የፈጸመውን የአገር ሕልውና የመናድ ጥቃት በመቀልበስ የአገር መከላከያ ሰራዊት አኩሪ ተግባር መፈጸሙ መገምገሙን ገልጸዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን ከሃዲው ቡድን በአማራ ክልል ላይ የከፈተውን ጥቃት በመመከት የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በተመሳሳይ አኩሪ ተጋድሎ መፈጸሙ በስራ አስጻሚው መገምገሙን ተናግረዋል።

በመሆኑም ፓርቲው ለአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ፣ ለአፋር ልዩ ኃይል እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለትግራይ ሕዝብ ምስጋናውን አቅርቧል።

የሕግ ማስከበር ዘመቻው በአጭር ጊዜ ስኬት ያመጣ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ብንናልፍ፤ “ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት አሸንፎ የወጣበት ነበር” ብለዋል።

በማይካድራ ፅንፈኛው የህወሃት ታጣቂ ሃይል በርካታ ዜጎችን ጭካኔ የተሞላበት ግድያ የፈፀመበት ሁኔታ በስራ አስጻሚው መገምገሙን ገልጸዋል።

ጁንታው በመተከል፣ በምዕራብ ወለጋና ጉራ ፈርዳ በውክልና ንጹሃንን ሲያስገድል መቆየቱንም ጠቁመዋል።

“ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ጠንካራ ብሔረ መንግስትና አገረ መንግስት በመገንባት ሂደት ውስጥ የሚስተዋሉ ዋልታ ረገጥና ጽንፈኝነትን መመከት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርጓል” ብለዋል አቶ ብናልፍ።

የትኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብና ልዩነት ቢኖርም በአገር ጉዳይ አንድ መሆን ስለሚያስፈልግ የዴሞክራሲ ምህዳሩን የማስፋት ስራ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ስራ አስፈፃሚው ተወያይቷል ተብሏል።

“የሕግ ማስከበር ዘመቻውን መሬት ማስመለስ አድርጎ የማቅረብ ሁኔታም መሰረተ ቢስ መሆኑ ተገምግሟል” ነው ያሉት።

“በወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ አካባቢ ያሉ ዜጎች ባለፉት 30 ዓመታት የፍትህ ጥያቄ ነበራቸው” ያሉት አቶ ብናልፍ፤ ''ማንነታቸውን የማንጸባረቅ ሰዋዊ ክብራቸውን ነው የጠየቁትም'' ብለዋል።

የሕወሓት ጁንታ እስካሁን በፈጸማቸው ወንጀሎች በሽብርተኝነት የሚያስፈርጀው ቢሆንም በሕግ ማስከበር ዘመቻው ለፍርድ የሚፈልጉ ግለሰቦችን ለህግ ማቅረብ የመንግስት ትኩረት እንደሆነ ጠቁመዋል።

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የብልጽግና ፓርቲ ለቀጣይ ምርጫ የሚጠቀምበት የመወዳደሪያ ማኒፌስቶ ላይም ሰፊ ውይይት አድርጓል ብለዋል አቶ ብናልፍ።

ቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ፓርቲው በተለየ መልኩ ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በቀጣይ በትግራይ ክልል በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት የተፈናቀሉትን ማቋቋም፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶችምን መጠገንና በጥቅሉ ክልሉን የማቋቋም ስራ እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።

1001001 Comment7 SharesLikeCommentShare

  • Ahmed Muheyeአዲስ ነገር ንገሩን?
    • Like
    •  · Reply
    •  · 5m
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም