ቀጥታ፡

የማረቆ ወረዳ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት 12 በሬዎችና 500 ኪሎ ግራም በርበሬ አበረከቱ

አዲስ አበባ ህዳር 26/2013 (ኢዜአ) በጉራጌ ዞን የማረቆ ወረዳ ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሠራዊት 12 በሬዎችና 500 ኪሎ ግራም በርበሬ ድጋፍ አበረከቱ።

የወረዳው ነዋሪዎች ተወካዮች በምድር ኃይል በመገኘት ስጦታውን ለመከላከያ ሚኒስቴር አስረክበዋል።

ተወካዮቹ እንደተናገሩት ነዋሪዎቹ ድጋፉን ያደረጉት ለአገር መከላከያ ሠራዊት አጋርነታቸውን ለመግለጽ ነው።

የማረቆ ወረዳ ዋና ስተዳዳሪ አቶ አወል ጁማቱ የጁንታው አባላት ለሕግ እስከሚቀርቡ ድረስ ድጋፉ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስቴር የግዥ ዳይሬክተር ብርጋዴል ጄኔራል ዓለምሰገድ ወንደሰን በሰሜን ዕዝ ላይ በተፈፀመው ክህደት የተቆጣው ሕዝብ ለሠራዊቱ ያለውን አጋርነት እየገለጸ መሆኑን ተናግረዋል።

የሕዝቡ ድጋፍና አጋርነት ሠራዊቱ ግዳጁን በሚገባ ለመፈጸሙ 'ትልቅ የሞራል ስንቅ' ሆኖታል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም