ቀጥታ፡

በሰራተኞች የጥቅማጥቅም ጥያቄ ምክንያት ተስተጓጉሎ የነበረው የአዲስ አበባ ባቡር ትራንስፖርት ሙሉ ለመሉ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ ሐምሌ 12/2010 በሰራተኞች የጥቅማጥቅም ጥያቄ ምክንያት ትናንት በከፊል ተስተጓጉሎ የነበረው የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መሉ በሙሉ ስራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ። የኮርፖሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተፈራ ለኢዜአ እንዳሉት የሰራተኞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ በመመለሱ ሰራተኞቹ ወደ መደበኛ ስራቸው ተመልሰዋል። ጥያቄዎችንም ከግምት በማስገባት የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች ከሰራተኞቹ ጋር ትናንት ሰፊ ውይይት ማድረጉንና ስምምነት ላይ መደረሱን ነው የጠቀሱት። ሠራተኞቹ ከምግብ አገልግሎት ዋጋ፣ አበል፣ ትርፍ ሠዓት ክፍያ፣ ደሞዝ ጭማሪና ከመኖሪያ ቤት ጋር በተያያዘ ጥያቄ አንስተው የነበረ ሲሆን የጥቅማጥቅም ጥያቄዎቹ በኮርፖሬሽኑ አቅም መሰረት ምላሽ አግኝቷል ብለዋል። በመሆኑም ከሃያት ጦር ሃይሎች አስራ አንድ ባቡሮች ከቃሊቲ ጊዮርጊስ ስምንት ባቡሮች ዛሬ ማለዳ ወደ መደበኛ ስራቸው መመለሳቸውን አቶ ደረጀ ተናግረዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም