ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 23/2012 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች የ2013 አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫን በተመለከተ ውይይት እያካሄዱ ነው።

ከውይይቱ አስቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የምርጫ ተዋናዮች ሚና እና የተለያዩ አገሮች የምርጫ ስርዓቶችን የሚመለከት የውይይት መነሻ ጽሑፍ አቅርበዋል።

እየተካሄደ ባለው ውይይት ተሳታፊዎች  መጪውን ምርጫ አስመልክቶ በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል።

ከተነሱት  ጉዳዮች  ለምርጫ  አስፈላጊ የሆኑ መሠረታዊ የሁኑትን አስቀድሞ ማሟላት፣ ከምርጫው አስቀድሞ የህግ የበላይነትን ማስከበር እንደሚገባና  የምርጫ ታዛቢዎችን ጨምሮ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚያገለግል የምርጫ ደንብን ማዘጋጀት  ይሚሉት ናቸው።
የሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተሳታፊነት ማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ  ሕግ መሠረት  ተሳታፊ መሆናቸውን ማረጋገጥ የሚሉ ጉዳዮች  ተነስቷል።  

በመድረኩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች  የሲቪክ ማህበረሰብ ተወካዮችና  የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ተገኝተዋል።

ውይይቱ ዐበይት ባለ ድርሻ አካላት ያላቸውን ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም የምርጫ ስርዓትን በሚያስቃኝ ገለጻ ተጀምሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም