መከላከያ ሰራዊት በአጭር ጊዜና በጥንቃቄ ባከናወነው ህግ የማስከበር ሂደት ተደስተናል- የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር - ኢዜአ አማርኛ
መከላከያ ሰራዊት በአጭር ጊዜና በጥንቃቄ ባከናወነው ህግ የማስከበር ሂደት ተደስተናል- የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር
አዲስ አበባ ህዳር 20/2013 (ኢዜአ) የአገር መከላከያ ሰራዊት በአጭር ጊዜና በጥንቃቄ የአገርን ህልውና በማስጠበቅ ባከናወነው ህግ የማስከበር ሂደት መደሰታቸውን ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ ተናገሩ።
የአገር መከላከያ ሰረዊት የህወሃትን እኩይ አላማ በማክሸፍ በአጭር ጊዜ ድል እየመታ መቀሌን መቆጣጠሩ ብቃቱንና ጀግንነቱን ያሳያል ብለዋል።
በህግ ማስከበር ሂደቱ ሰላማዊ ዜጎች ጉዳት ሳይደርስባቸውና ለቅርሶች ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ መከናወኑም አስደስቶናል ብለዋል።
በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ በእልህና ጀግንነት ለተሳተፉ የፀጥታ ሃይሎችም አክበሮታቸውን ገልጸዋል።
በሚኒስትሯ በተቋሙ ሰራተኞችና በራሳቸው ስም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክታቸውንም አስተላልፈዋል።
በተያያዘ ዜና የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ እና የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞችም የደስታ መግለጫ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ድል ላደረገው የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ሚሊሻም ምስጋና እና ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።