ጁንታው የግንባሩን መሪ ይቅርና አንድ ወታደር መማረክ አይችልም፤ እኔን የሚማርከኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነው -- ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ - ኢዜአ አማርኛ
ጁንታው የግንባሩን መሪ ይቅርና አንድ ወታደር መማረክ አይችልም፤ እኔን የሚማርከኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነው -- ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ
ህዳር 20/2013 (ኢዜአ) "ጁንታው የግንባሩን መሪ ይቅርና አንድ ወታደር መማረክ አይችልም፤ እኔን የሚማርከኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነው" ሲሉ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ።
የህወሓት ጁንታዎች የጦር መሳሪያ በመዝረፋቸውና ሚኒሻ በማስታጠቃቸው ብቻ እናሸንፋለን ብለው ማሰባቸው "ጅሎች" መሆናቸውን የታዘብንበት አጋጣሚ ነው ብለዋል።
ሌተናል ጀነራል ባጫ በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን ተራሮች ላይ በሰጡት መግለጫ ጁንታው "እየተመታ ማርከናቸዋል፤ እየተሸነፈ ደግሞ አሸንፈናል በማለት ውሸቱን ቀጥሎበታል ብለዋል።
በሶስተኛው ዙር ኦፕሬሽን መቀሌን ከተቆጣጠርን በኋላ የማረጋጋትና የማቋቋም ስራ እየተከናወነ መሆኑንን የገለፁት ሌተናል ጀነራል ባጫ ጁንታውን ካቴና አስገብተንለት ወደ ፍርድ ቤት ማቅረባችንም የማይቀር ነው ብለዋል።
"በአፋቸውና በምላሻቸው ኒውክሌር የታጠቁት የጁንታው ቡድን አባላት መግቢያና መውጫ አጥተው ሰው ማረከን ማለታቸው እንዳስገረማቸውም ገልጸዋል።
ውጊያና ጦርነት ምን እንደሆነ ስለማያውቁ የግንባሩን ወታደር ሳይቀርቡ የግንባሩን መሪ ማረክን የሚሉ የዋሆች በማለት ግርምታቸውን ጠቅሰዋል ።
"ጁንታው የግንባሩን መሪ ይቅርና አንድ ወታደር መማረክ አይችልም፤ እኔን የሚማርከኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
እነሱ የፈለጉትን ያውሩ እኛ ግን ካቴና አስገብተን ወደፍርድ ቤት እናቀርባቸዋለን ሲሉም አረጋግጠዋል።
የጁንታው ቡድን "ከመከላከያ ሰራዊቱ 30 ታንክና ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌን ማረክን" የሚል የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሲያናፈሱ አንደነበር ይታወቃል።