ወደ ሁለተኛ አገራችን ኢትዮጵያ መምጣታችን ልዩ ስሜት ፈጥሮብናል-ኤርትራዊያን - ኢዜአ አማርኛ
ወደ ሁለተኛ አገራችን ኢትዮጵያ መምጣታችን ልዩ ስሜት ፈጥሮብናል-ኤርትራዊያን
አዲስ አበባ ሀምሌ 11/2010 ወደ ሁለተኛ አገራቸው ኢትዮጵያ መምጣታቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ኤርትራዊያን ተናገሩ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሁለት አስርት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መንገደኞችን ከአስመራ አዲስ አበባ አጓጉዟል። ኤርትራዊያኑ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ሰራተኞች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው ኤርትራዊያን በዚሁ ወቅት በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን ገልፀው ወደ ሁለተኛ አገራቸው ኢትዮጵያ መምጣታቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረላቸውም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ ከአስመራ- አዲስ አበባ ሁለት በረራዎችን ማድረጉ ይታወሳል።