በአማራ ክልል ከ865 ሺህ ለሚበልጡ ህጻናት የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ሊሰጥ ነው

63

ባህርዳር፣ ህዳር 17/2013(ኢዜአ) ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ከ865 ሺህ በላይ ህጻናትን ተጠቃሚ የሚያደረግ የፖሊዮ (የልጅነት ልምሻ) መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የቅኝት ሰርቬላንስና የተጋላጭነት ልየታ ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ አሌ አያል ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ክትባቱ የሚሰጠው በክልሉ ሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር፣ ደቡብ ወሎ ዞኖችና ደሴ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ህጻናት ነው።

ለአራት ቀናት በሚካሄደው የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ዕድሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ 865 ሺህ 284 ህጻናት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ጠቁመው፤ ለዚህም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

ለዘመቻው መሳካት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ትብብር እንዲያደርጉ አስተባባሪው መልዕክታቸውን አሰተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም