ቀጥታ፡

አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ለአፍሪካ አምባሳደሮች ገለፃ አደረጉ

ህዳር 17/2013 (ኢዜአ) በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ማርቆስ ተክሌ መንግስት በትግራይ እያካሄደ ስለሚገኘው የሕግ ማስከበር ዘመቻ አስመልክቶ መቀመጫቸውን ካይሮ ላደረጉ የአፍሪካ አምባሳደሮች ገለፃ አድርገዋል።

አምባሳደር ማርቆስ ባደረጉት ገለፃ የመንግስት የህግ አስከባሪ ስራን አስፈላጊነት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የፌዴራሉ መንግስት እምቢተኛውን የህወሃት ቡድን በውይይት ውስጥ ለማሳተፍ ያደረጋቸው ተደጋጋሚ ሙከራዎች እንዳልተሳኩ አስረድተዋል፡፡

የጁንታው ህወሃት ቡድን ሀገር እንዳትረጋጋ በመስራት የሀገሪቱን ህገ-መንግስት ስጋት ላይ የጣለ እንቅስቃሴ፤ የፌደራል መንግስት የህግ ማስከበር ዘመቻውን እንዲጀምር እንዳስገደደው ገልጸዋል።

በተጨማሪም አምባሳደር ማርቆስ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለው የሕግ ማስከበር ሥራ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ በሆነችበት የህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ምንም አይነት ተፅዕኖ አይኖረውም ነው ያሉት።

ምንጭ-በካይሮ የኢፌዴሪ ኢምባሲ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም