ቀጥታ፡

የመከላከያ ሠራዊት ልዩ ስሙ ሰላስል በተሰኘው የሐውዜን ተምቤን መገንጠያ መንገድ የገጠመውን የጁንታውን ኃይል ድል አድርጓል

ህዳር 13/2013 (ኢዜአ) የመከላከያ ሠራዊት በአድዋ ተምቤን መሥመር ማይቅናጥል በተባለውና ልዩ ስሙ ሰላስል በተሰኘው የሐውዜን ተምቤን መገንጥያ መንገድ የገጠመውን የጁንታውን ኃይል ድል አድርጓል።

በዚሁ መገንጠያ ላይ የሠራዊቱን ግሥጋሴ ለመግታት በኮሎኔል ጸጋዬ ማርክስና በኮሎኔል ሸሪፎ የሚመራው የጁንታው አንድ ክፍለ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል ፡፡

የመከላከያ ዘመቻ ዋና መመሪያ ማምሻውን እንዳስታወቀው የመከላከያ ሠራዊታት ክፍለ ጦሩን ሙሉ በሙሉ ከደመሰሰ ቡኋላ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም