ቀጥታ፡

የአገር መከላከያ ሰራዊት አዲግራትን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ መቀሌ እያመራ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12/2013 (ኢዜአ) የአገር መከላከያ ሰራዊት አዲግራትን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ መቀሌ እያመራ መሆኑን ¬የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ገለጸ።

“ዛሬ ኅዳር 12 2013 አዲግራት ከሕወሓት ጁንታ ነጻ ወጣች” ሲል ገልጿል።

“የመከላከያ ሠራዊታችን ዛሬ በጠዋቱ የሕወሓትን ጁንታ ኃይል ድል አድርጎ የአዲግራት ከተማን ሙሉ በሙሉ ነጻ አውጥቶ
የመከላከያ ሠራዊታችን በአሁኑ ጊዜ ወደ መቀሌ እያመራ ነው” ብሏል።

ትናንት ማምሻውን ሰራዊቱ አክሱም፣ አድዋንና አዲግራት ዙሪያን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም