ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደማቸውን ለገሱ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 11/2013 (ኢዜአ)  ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደማቸውን ለግሰዋል።

ለሰራዊቱ 5 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍም አድርገዋል።

የድርጅቱ አመራሮችና ሰራተኞች ''ደሜ ለአገር መከላከያ ሰራዊት'' በሚል መርህ ነው በዛሬው እለት ደማቸውን የለገሱት።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በመርሃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ለአገር ህልውና ሕይወቱን እየሰጠ ላለው መከላከያ ሰራዊት ደም መለገስና ድጋፍ ማድረግ ከዜጎች ይጠበቃል ብለዋል።

የተጀመረው ሕግ የማስከበር ተግባር እስኪጠናቀቅ ዜጎች ከመንግሥት ጎን በመሆን ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩም ጠይቀዋል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ የሺመቤት ነጋሽ በበኩላቸው የድርጅቱ አመራሮችና ሰራተኞች ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያቸውን ክብርና አጋርነት ለመግለፅ የደም ልገሳ ማድርጋቸውን ገልጸዋል።

ሰራተኞቹ ከደም ልገሳው በተጨማሪ ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም ድርጅቱ 5 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፎችን አድርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም