ቀጥታ፡

የመከላከያ ሠራዊት አክሱምን፣ አድዋንና የአዲግራትን ዙሪያ ተቆጣጠረ

ህዳር 11/2013(ኢዜአ) የመከላከያ ሠራዊት ዛሬ ህዳር 11/2013 ዓ.ም አክሱምን፣ አድዋንና የአዲግራትን ዙሪያ ተቆጣጠረ።

በምዕራብ ግንባር የሕወሐት ጁንታን ኃይል እያጠቃ ያለው የመከላከያ ሠራዊት፣ ከሽሬ በኋላ ሰለህለሃ ላይ የመሸገ የሕወሐት ኃይል ገጥሞት እንደነበር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪ አሳውቋል።

ሰለህለሃ ላይ የመሸገው የጁንታው ኃይል መንገዱን በዶዘር ቆርጦና አስፓልቱን አበላሽቶ በቦታው ከባድ መከላከል ማድረጉም ተገልጿል።

የመከላከያ ሠራዊቱ የጁንታውን ተከላካይ ኃይል ሠብሮ በመግባት አክሱምን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

ከአክሱም ወደ አድዋ በነበረው ጉዞ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የጁንታው ኃይል ለመከላከል ቢሞክርም፣ በመከላከያ ሠራዊቱ ድል ሆኗል ነው የተባለው።

መከላከያ እንቲጮንና የአዲግራትን ዙሪያ ተቆጣጥሮ ወደ አዲግራት ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል መሆኑም ተጠቅሷል።

አያሌ የጁንታው ተዋጊዎች እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ከድተው ከጁንታው ጋር ሆነው ሲዋጉ የነበሩ ወታደሮችም እንደሚገኙበትም ነው የተገለጸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም