ቀጥታ፡

በመጪው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የመገናኛ ብዙሃን ድልድል ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11/2013 (ኢዜአ) ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የመገናኛ ብዙሃን ድልድል ረቂቅ መመሪያ ላይ ከመገናኛ ብዙሃንና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ ነው።

የውይይቱ ዓላማ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ቀደም ሲል በተካሄዱ ምርጫዎች በመገናኛ ብዙሃን ቅስቀሳ ሲያቀርቡ ያጋጠማቸውን ችግሮች በማንሳት ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ፍትሃዊና ሚዛናዊ አሰራር ለመዘርጋት ነው።

ረቂቅ መመሪያው ለመድረኩ ተሳታፊዎች ቀርቦ አስተያየት የሚሰበሰብ ይሆናል።

ምርጫ ቦርድ በሚያወጣው መመሪያና በሚወስነው የድልድል መስፈርት መሰረት ድልድሉ በሶፍትዌር በመታገዝ እንደሚከፋፈልም ተገልጿል።

በዛሬው መድረክ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የአሰራር ስርዓት ላይ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም