የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ 76 ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ

102

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9/2013 (ኢዜአ) የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ 76 ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በትግራይ ክልል በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም አገር የማፍረስ ሴራ አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና የአገር ክህደት ወንጀል የፈፀሙ የጁንታው ህዋሃት የበላይ አመራሮችን ለሕግ ለማቅረብ ሕዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደወጣባቸው መገለፁ ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይ ከጁንታው የህዋሃት ቡድን አባላት ጋር እየተገናኙ አገር በማፍረስ ሴራ ውስጥ በመሳተፍ የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የአገር መከላከያ ሠራዊት ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች እንዲሁም የፖሊስ አመራሮች ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ኮሚሽኑ አስታውሷል።

በዛሬ መግለጫውም በህዋሃት የጥፋት ቡድን አገር የማተራመስና የማፍረስ ሴራ እጃቸውን ባስገቡና በአገር ክህደት ወንጀል የተሳተፉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት በአገር መከላከያ ሠራዊት በስራ ላይ ያሉና በጡረታ የተሰናበቱ ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች የተጣለባቸውን ሕዝባዊና አገራዊ አደራና ኃላፊነት ወደ ጎን በመተውና የጁንታው የህወሃት ቡድን የሴራ አካል በመሆን የአገር ክህደት ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን ለሕግ ለማቅረብ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ገልጿል።

ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶቹ ከአገር መከላከያ ሠራዊት እሴቶች መካከል ከራስ በፊት ለሕዝብና ለሀገር ጥቅም የሚለውን ወደ ጎን በመተው የወንበዴው ህዋሃት የሴራ አካል በመሆን በወንጀል የሚፈለጉ መሆናቸውንም አመልክቷል።

በመሆኑም መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች በተለይም ደግሞ የትግራይ ሕዝብ፣ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላትና ሚሊሻዎች፤ የአገር መከላከያና የፖሊስ ሠራዊቶች እንዲሁም የደህንነት ተቋማት እነዚህን ተፈላጊዎች አድኖ ለሕግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ጥረት በያላችሁበት የድርሻችሁን እንድትወጡ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

በቀጣይም በጁንታው የህዋሃት የጥፋት ቡድን አገር የማተራመስና የማፍረስ ሴራ እንዲሁም በአገር ክህደት ወንጀል የተሳተፉትንና በየትኛውም የኃላፊነት ደረጃና መዋቅር ላይ ያሉ ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ስራውም ሆነ በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

የአገር ህልውናን አደጋ ላይ በመጣልና ሕገ-መንግስቱንና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል በመናድ ወንጀል በመሳተፍ የሚፈለጉትና የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው በስራ ላይ ያሉና በጡረታ የተሰናበቱ የአገር መከላከያ ሠራዊት ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶችን ስም ዝርዝርም አውጥቷል።

1.ሜጀር ጄኔራል ማህሾ በየነ 2.ሜጀር ጄኔራል መሀመድ አይሻ ዘይኑ 3.ሜጀር ጄኔራል ሙሉ ግርማይ ገ/ህይወት 4.ሜጀር ጄኔራል ሀለፎም እጂጉ 5.ብርጋዴል ጄኔራል ፍትዊ ፀሃዬ ገ/እግዚአብሔር 6.ብርጋዴል ጄኔራል ግደይ ሀይሉ ገ/እግዚአብሔር 7.ብርጋዴል ጄኔራል ነጋሽ ዳኘው8.ብርጋዴል ጄኔራል መብራቱ ወ/አረጋይ 9.ብርጋዴል ጄኔራል ወልደ ጊዮርጊስ10. ብርጋዴል ጄኔራል አብዲሳ ፍላንሳ11. ብርጋዴል ጄኔራል ጉሽ ገብሬ12. ብርጋዴል ጄኔራል ከበደ ፍቃዱ13. ብርጋዴል ጄኔራል ገብረጊዮርጊስ14. ብርጋዴል ጄኔራል ህንፃ ወ/ገወርጊስ15. ኮሎኔል ተወልደ ገ/ትንሳይ16. ኮሎኔል ንጉሴ ገብሩ17. ኮሎኔል መብራቱ አሰፋ /አልማዝ/18. ኮሎኔል ዘገየ ንጉስ19. ኮሎኔል ያለም20. ኮሎኔል መብራቱ ተድላ21. ኮሎኔል ነጋሽ መብራቱ22. ኮሎኔል ተክሉ በላይ23. ኮሎኔል ጥጋቡ መለስ24. ኮሎኔል ግርማ ተካ25. ኮሎኔል ሙሉጌታ ገብረክርስቶስ ነጋሽ26. ኮሎኔል አራሞ ገ/መድህን27. ኮሎኔል ተስፋዬ ገ/መድህን28. ኮሎኔል ግርማል አለማየሁ29. ኮሎኔል ነጋሽ አለፎም30. ኮሎኔል ተስፋዬ ምሩፅ31. ኮሎኔል ካሳየ አሰፋ32. ኮሎኔል ነጋሲ ታደሰ ስዩም33. ኮሎኔል ኪሮስ ሓጎስ ገ/ዝጋብሔር34. ኮሎኔል ሙርፅ ገብረሊባኖስ አብርሃ35. ኮሎኔል ሓ/ስላሴ ኪሮስ ተስፋይ36. ኮሎኔል ምሩፅ በርሔ/ተወርወር/37. ኮሎኔል ሀይለስላሴ አሰፋ38. ኮሎኔል ደርበው ኃጎስ39. ኮሎኔል ወልዴ ሀጎስ40. ኮሎኔል ንጉሴ አማረ41. ኮሎኔል ነጋሲ ታደሰ42. ኮሎኔል ባራኪ /ወዲ ራያ/43. ኮሎኔል ከበደ ገ/ሚካኤል44. ኮሎኔል ፀጋ ብርሀን ገ/እዜር45. ኮሎኔል ዘሩ ሀ/መለኮት46. ኮሎኔል ሀይለ መዝገብ47. ኮሎኔል አርአያ ገብሩ ግደይ48. ኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል49. ኮሎኔል ዘሩ መረሳ50. ኮሎኔል ልጃለም ገ/ህይወት51. ኮሎኔል አስመላሽ ወልዴ52. ኮሎኔል ፍሰሀ ግደይ53. ኮሎኔል አምባቸው ወ/ገብርኤል54. ኮሎኔል ገብረመስቀል ወልደገብርኤል55. ኮሎኔል ወልዱሀጎስ ገብሩ56. ኮሎኔል ገ/ሚካኤል ሀጎስ57. ኮሎኔል ስብሀቱ መብራቱ58. ኮሎኔል ጣሰው ወ/ጊዮርጊስ59. ኮሎኔል ገ/እግዚያብሔር አለምሰገድ60. ኮሎኔል ነጋሲ ታደሰ61. ኮሎኔል ተክለ በላይ62. ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ አብርሃ ወ/ሚካኤል63. ሌተናል ኮሎኔል ሙዘይ ተሰማ ስዩም64. ሌተናል ኮሎኔል ሀዲሽ ገብረፃድቅ አለማየሁ65. ሌተናል ኮሎኔል ፍስሃ በየነ ገ/ኪዳን66. ሌተናል ኮሎኔል ምሩፅ ወ/አረጋይ ገ/መስቀል67. ሌተናል ኮሎኔል ሙሩፅ በርሀ ኣበራ68. ሌተናል ኮሎኔል ፀሀዬ ሀጎስ69. ሌተናል ኮሎኔል ሀጎስ ኪሮስ70. ሌተናል ኮሎኔል ገብረ ህንፃ ሀዲሽ71.ሌተናል ኮሎኔል ገብረመድህን ወ/ማርያም አሉላ72. ሌተናል ኮሎኔል ፈለቀ አይጠገብ73. ሻለቃ አስገዶም መስፍን74. ሻምበል ባሻ ሙእዝ መልካም75. ሻምበል አርአያ ተ/ኃይማኖት76. ሻምበል ተስፋ ህይወት ………ናቸው ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም