የአፍሪካ የሰላም ተምሳሌት የሆነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ክብር ይገባዋል-- የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ የሰላም ተምሳሌት የሆነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ክብር ይገባዋል-- የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር
አዲስ አበባ ህዳር 8/2013 (ኢዜአ) የአፍሪካ የሰላም ተምሳሌት የሆነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የተሰጠው ክብር ሁሉንም ያስደሰተ መሆኑን የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚንስትር ፊልሰን አብዱላሂ ገለጹ።
የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚንስቴር ሰራተኞችና አመራሮችና ሰራተኞች "ለመከላከያ ሰራዊታችን ክብር እንቆማለን´" በሚል የተዘጋጀውን መርሃ ግብር አክብረዋል።
ሚንስትሯ ፊልሰን አብዱላሂ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የመላ አፍሪካ የሰላም ተምሳሌት ነው።
በመሆኑም ሰራዊቱ በሚገባው ልክ ክብርና ሞገስ ሊሰጠው ይገባል እንጂ ክህደትና ሴራ ሊፈፀምበት አይገባም ነበር ብለዋል።
በህወሃት ፅንፈኛ ሃይል የተፈፀመበት ክህደትም የሰራዊቱን ውለታ የካደና አገርን ለአደጋ የሚያጋልጥ እኩይ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም በዛሬው እለት ለአገር መከላከያ የተሰጠው ክብርና ፍቅር ሁሉንም ያስደሰተና የሚገባው ሆኑን ነው የተናገሩት።
የሚኒስቴሩ ሰራተኞችም እለቱን በማሰብ ለሰራዊቱ ፍቅርና አብሮነታቸውን በማሳየት አክብረውታለ።
በተያያዘ ዜና የአራዳ ክፍለ ከተማ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ሰራተኞች እለቱን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አስበውታል።
በእለቱ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ወጣቶች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተከናውኗል።
በክፍለ ከተማው የኪነ-ጥበብ ቡድን አባላት ድራማ፣ ሽለላ፣ ቀረርቶ፣ ግጥም እና መነባንብ በማቅረብም ለአገር መከላከያ ሰራዊቱ ክብራቸውን አሳይተዋል።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሠራተኞችም እለቱን ለአገር መከላከያ ሰራዊት ክብር በመስጠት አብሮነታቸውን አሳይተዋል።