ቀጥታ፡

ለአገር መከላከያ ሰራዊት የምናደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል- የሃላባ ዞን ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7/2013 (ኢዜአ) የህግ ማስከበር ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ለአገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከሃላባ ዞን የተወከሉ አባቶች ተናገሩ።

የሃላባ ዞን ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሰራዊት 6 ሚሊዮን ብር እና የእርድ እንስሳትን ድጋፍ አድርገዋል።

በደቡብ ክልል የሃላባ ዞን ነዋሪዎች በትግራይ የህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሰራዊት 6 ሚሊዮን ብር እና የእርድ እንስሳትን ድጋፍ አድርገዋል።

ከዞኑ ተወክለው የመጡ አባቶች እንዳሉት ድጋፉን ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት ምድር ሃይል በመገኘት አስረክበዋል።

የዞኑ ነዋሪዎች 6 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ ካደረጉት ድጋፍ በተጨማሪ 255 ሰንጋዎች እና 36 በግና ፍየሎችን አበርክተዋል።

የዞኑ ማህበረሰብ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን እንደሆነ ገልጸው፤ በቀጣይም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁነት እንዳላቸው አረጋግጠዋል።

የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰራዊቱ ያለውን ድጋፍ እያሳየ መሆኑን ገልጸው፤ ለተደረገው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

የሃላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር መሀመድ ኑርዬ፤ የዞኑ ነዋሪዎች በአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የህወሃት ዘራፊ ጁንታ አማካኝነት የደረሰውን እኩይ ተግባር የዞኑ ነዋሪዎች ማውገዛቸውን ገልፀዋል።

በትላንትናው ዕለትም የዞኑ ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ድርጊቱን ማውገዛቸውን ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለትም የዞኑ ነዋሪዎች ለሰራዊቱ ያላቸውን ድጋፍና አብሮነት ለማረጋገጥ ድጋፍ ማድርጋቸውን ገልጸዋል።

የሃላባ ዞን ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።

ከዞኑ ተወክለው ድጋፉን ለመከላከያ ሚኒስቴር ካስረከቡት መካከል ሃጂ ገራድ ድልታታ እንዳሉት ህወሃት በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመው ጥቃት የአገር ክህደት መፈፀሙን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

ሃጂ ዩሱፍ ሁሴን የተባሉት ተወካይ ደግሞ የትግራይ ህዝብን የማይወክሉ ጥቂት ቡድኖች በፈፀሙት ተግባር ሁላችንም አዝነናል ብለዋል።

ወጣቶችን ወክሎ የተገኘው ሀሩና አህመድም የህወሀት ዘራፊ ቡድን ለ27 ዓመታት አገሪቱን ሲዘርፍ ዜጎችን ሲገድል እና ሲያሳድድ የኖረ ጽንፈኛ ቡድን መሆኑን ተናግሯል።

ቡድኑን ለማስወገድ በአገር መከላከያ ሃይል እየተወሰደ ያለው የህግ ማስከበር ዘመቻ እስኪጠናቀቅ የዞኑ ወጣቶች ድጋፍ እንደማይለይ አረጋግጧል።

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡ ሲሆን ምስጋናቸውንም አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም