ኢትዮጵያና ኤርትራ በየብስ የሚገናኙበት ዕድል በአፋጣኝ እንዲመቻችላቸው የሁለቱ አገራት ዜጎች ጠየቁ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያና ኤርትራ በየብስ የሚገናኙበት ዕድል በአፋጣኝ እንዲመቻችላቸው የሁለቱ አገራት ዜጎች ጠየቁ
ሁመራ ሀምሌ 10/2010 በኢትዮጵያና በኤርትራ መንግስታት መካከል የተፈጠረውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሁለቱ አገራት ወንድማማች ህዝቦች በየብስ የሚገናኙበት ዕድል በአፋጣኝ እንዲመቻችላቸው በድንበር አካባቢ ያሉ የሁለቱ አገራት ዜጎች ጠየቁ። የሁለቱም መንግስታት መቀራረብና የሰላም ስምምነትን ተከትሎ በድንበር አካባቢዎች የሚኖሩ የሁለቱም አገራት ዜጎች በተከዜ ድልድይ በኩል በቅርብ ርቀት መገናኘት መጀመራቸውን ተናግረዋል። በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የሰቲት-ሑመራ ነዋሪ አቶ ዮሴፍ አብርሃ "የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች ወድማማች ህዝቦች በመሆናችን ሰላምን አጥብቀን እንሻለን" ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል። "በአሁኑ ወቅት የሁለቱ አገራት መሪዎች ተቀራርበው የሰላም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ትልቅ እድል ነው" ያሉት አቶ ዮሴፍ፣ አገራቱ ቀደም ሲል በገቡት ቅራኔ ምክንያት የሚያዋስናቸው የተከዜ ወንዝ ዳርቻና ድልድይ ለ20 ዓመታት ተዘግቶ መቆየቱን ተናግረዋል።
አገራቱ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በአሁኑ ወቅት የደረሱበትን ስምምነት ተከትሎ ወደተከዜ ወንዝ ዳርቻ በማምራት ነባራዊውን ሁኔታ ሰሞኑን መቃኘታቸውን የገለጹት አቶ ዮሴፍ፣ በተመሳሳይ ኤርትራውያንም ወደወንዙ ዳርቻ በመምጣት በቅርብ ርቀት ሰላምታ መለዋወጥ መጀመራቸውን ተናግረዋል። "ሁለቱም ህዝቦች እርስ በርስ በየብስ መገናኘት እንዲችሉ የሁለቱ አገራት መንግስታት የደረሱበትን ስምምነት ሙሉ ለሙሉ በመተግበር በኩል ሊያፋጥኑ ይገባል" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ሌላው የሰቲት ሑመራ ወረዳ ነዋሪ ወጣት ሰሎሞን በርሄ በበኩሉ በአቅራቢያቸው የምትገኘውንና የኤርትራ ከተማ የሆነችውን እምሐጀር ከተማን ለማየት መጓጓቱን ተናግሯል። የሁለቱን አገራት ድንበር ጠባቂዎችን በማስፈቀድ ወደተከዜ ወንዝ ድልድይ ከመጡ ኤርትራውያን መካከል አቶ ዘርአጽዮን መሀሪ በበኩላቸው "ከሦስት ቀን በፊት የሁለቱን አገራት ሰንደቅ ዓላማ ይዘን ወደ ተከዜ ድልድይ በመምጣት ከኢትዮጵያውያን ውንድሞቻችን ጋር ለመገናኘት ሞክረን ሳይሳካ ቀርቷል" ብለዋል። "የሁለቱም አገራት ህዝቦች የምንጋራው የጋራ ሰላም፣ ባህልና እሴት ስላለን ግንኙነታችንን የማጠናከር ፍላጎት አለን " ብለዋል። " እኛ ሰላምን ነው የምንፈልገው፣ ከተቀራረብን በጋራ ልንጠቀም እንችላለን " ያሉት አቶ ዘርአጽዮን ህዝብን ለህዝብ መቀራረብ ከተቻለ የጋራ ችግሮችን በቀላሉ መፍታት እንደሚቻል አመልክተዋል። ሐምሌ 11ቀን 2010 ዓ.ም በአገራቱ መካከል የሚጀመረው የአየር ትራንስፖርት ግንኙነት ህዝብ ለህዝብን ለማስተሳሰር ጠቀሜታው የጎላ ቢሆንም የየብስም ትራንስፖርት ግንኙነትም በአፋጣኝ እንዲጀመር ጠይቀዋል። " ኢትዮጵያን እንደ አገሬ ነው የማያት፤ በሁለቱ አገራት መካከል በነበረው ቅራኔ ምክንያት ለዓመታት ከቤተሰቦቼ ተነጥዬ ቆይቻለሁ" ያሉት ደግሞ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ሰቲት ሑመራ የሚኖሩት ኤርትራዊው አቶ የማነ ተስፋሚካኤል ናቸው። አሁን በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተፈጠረው ሰላም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በአካል ለመገናኘት መጓጓታቸውን ገልጸው የሁለቱ አዋሳኝ አካባቢ ህዝቦችን የሚያገናኝ የተከዜ ወንዝ ድልድይ መክፈትን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። የተከዜ ወንዝ ድልድይ የሁለቱን አገራት ህዝቦች ሲያገናኝ የነበረ ታሪካዊ ድልድይ መሆኑ ይታወቃል።