በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ናይሮቢ ገባ - ኢዜአ አማርኛ
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ናይሮቢ ገባ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 7/2013 (ኢዜአ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ ናይሮቢ ገብቷል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቆይታቸው ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
አቶ ደመቀ መኮንን ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ጋር በተለይም መንግስት በትግራይ ክልል የጀመረውን ህግ የማስከበር ዘመቻ እንደሚያስረዱ በኬንያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል።
መንግስት የጀመረውን ህግና ህገ መንግስት የማጽናት ጥረት እንዲደግፉ ለማስቻል የጠቅላይ ሚንስትሩን መልዕክት የያዘና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን በቀጠናው አገራት ጉብኝት ጀምሯል።
አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ ከዩጋንዳው ፕሬዝደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።
44