የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ኦቪድ ኮንስትራክሽን ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ኦቪድ ኮንስትራክሽን ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 7/2013 (ኢዜአ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ኦቪድ ኮንስትራክሽን ለአገር መከላከያ ሠራዊት 30 ሰንጋዎችን እና 60 ፍየልና በጎችን አበረከቱ።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በትግራይ የህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት ያለውን አጋርነት ለመግለጽ ያደረገውን የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ዛሬ ለመከላከያ ሚኒስቴር አስረክቧል።
ድጋፉን ያስረከቡት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ጀማል የህወሓት ጁንታ ቡድን በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የፈጸመውን አስነዋሪ ድርጊት አውግዘው፣ "የተደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል" ብለዋል።
በተያያዘም ኦቪድ ኮንስትራክሽን ግምታቸው 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሆኑ 30 ሰንጋዎች እና 60 ፍየልና በጎችን ለአገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አድርጓል።
የኦቪድ ኮንስትራክሽን ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ ታደሰ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ድርጅታቸው ለመከላከያ ሠራዊቱ ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ የተደረጉትን ድጋፎች በመረከብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ለሠራዊቱ ያለውን ድጋፍና አጋርነት እያሳየበት ያለው ተግባር ሁሉንም ያኮራ መሆኑንም ገልጸዋል።
ሁለቱ ተቋማት ያደረጉት ድጋፍ በድምሩ 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚገመት መሆኑም ታውቋል።