ቀጥታ፡

"የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በኡጋንዳ ከህወሃት ጋር በሽምግልና ውይይት ይሳተፋሉ" የሚለው መረጃ ሐሰተኛ ነው - የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ

አዲስ አበባ ህዳር 7/2013 (ኢዜአ) "የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በኡጋንዳ ከህወሓት ጋር በሽምግልና ውይይት ይሳተፋሉ" የሚለው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ገልጿል። 

መገናኛ ብዙሃን ያልተጣራ መረጃ ለኅብረተሰቡ ከማድረስ መቆጠብ አለባቸውም ብሏል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በኡጋንዳ ከሕወሓት ጋር በሽምግልና ውይይቶች ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በተለያዩ የዜና አውታሮች የቀረበው መረጃ የተሳሳተና በአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ግብረ ኃይል ያልተረጋገጠ መሆኑን ነው ያስታወቀው።

የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሠራ እንደሚገኝም ገልጿል።

የመገናኛ ብዙሃን አካላት እንደ መሠረታዊ የጋዜጠኝነት አሠራር የኢትዮጵያን የሕግ የበላይነትን ማስከበር  የሚመለከቱ ጥያቄዎችን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ኃይል ፕሬስ ሴክሪታሪያት በኩል እንዲያረጋግጡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ጥሪውን አቅርቧል።

"የህወሓት ቡድን"  ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ መንግስት ለአገር መከላከያ ሠራዊት በሰጠው የሕግ ማስከበርና አገርን የማዳን ተልዕኮ ሠራዊቱ የዘመቻ ስራውን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም