ቀጥታ፡

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ግብረ ሃይል ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፉን ለመግለጽ መርሐ ግብር ማዘጋጀቱን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5/ 2013 (ኢዜአ) የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ግብረ ሃይል ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፉን ለመግለጽ የፊታችን ማክሰኞ የሚከወን መርሐ ግብር ይፋ አደረገ።

መርሃ ግብሩ ህዳር 8 ቀን 2013 ረፋድ 5፡30 ላይ "ለአገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ" በሚል መሪ ቃል በአገር ውስጥና በውጭ አገር ኢትዮጵያውያን ዘንድ የሚከወን ነው።

መርሐ ግብሩም ለአንድ ደቂቃ ከመሪዎች ጀምሮ ሁሉም ዜጋ በያለበት ሆኖ ከቤቱ ደጃፍ በመውጣት እጁን ልብ ካለበት ቀኝ እጅን በግራ ደረት ላይ በማንበር ክብር ይሰጣሉ።

በመጨረሻም ለአንድ ደቂቃ በጭብጨባ ክብሩን ይገልጻል፤ አሽከርካሪዎች በመኪኖች ድምፅ፣ ሌላው ህዝብም በድምፅ ማጉያዎች ለሰራዊቱ ያለውን ድጋፍ ይገልጻል ተብሏል።

በዕለቱ የአገር መሪዎች በአንድነት ፓርክ የሚሳተፉ ሲሆን በተለያዩ የአዲስ ከበባ ከተማ አካባቢዎች የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ባሉበት የማርሽ ባንድ ዝግጅቶች ይከወናሉ።

በቅርቡ ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፍ ለመስጠት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ግብረ ኃይል መቋቋሙ ይታወቃል።

ከህዳር 8ቱ መርሐ ግብር በተጨማሪ ሌሎች ዝግጅቶች ይደረጋሉ።

ግብረ ሃይሉ በህወሃት ቡድን በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በጽኑ አውግዟል።

22

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም