ቀጥታ፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ ተግባራዊ የሚሆን ደንብ አጸደቀ

አዲስ አበባ ህዳር 3/2013 (ኢዜአ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ ተግባራዊ የሚሆን ደንብ አጸደቀ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 (9) እና የፌዴራል መንግሥት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀፅ 14/2/ለ/ መሠረት የትግራይ ብሔራዊ ክልልን በጊዜያዊነት የሚያስተዳድር፤ ለፌዴራል መንግሥቱ ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም መወሰኑ ይታወቃል። 

በዚህ መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት “በትግራይ ብሔራዊ ክልል የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ” ተግባራዊ የሚሆን ደንብ ማፅደቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ገጻቸው አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም