የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በተጨማሪ 2 ቋንቋዎች ተደራሽ ሊሆን ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በተጨማሪ 2 ቋንቋዎች ተደራሽ ሊሆን ነው
አዲስ አበባ ህዳር 3/2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በተጨማሪ ሁለት ቋንቋዎች ተደራሽ ለመሆን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ በአራት ቋንቋዎች የተለያዩ ጋዜጦችን በማዘጋጀት ለተገልጋዮች ሲያደርስ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
አሁን በሲዳምኛና በትግሪኛ ቋንቋዎች ተደራሽ ለመሆን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
በሲዳምኛ ቋንቋ "በካልቻ" በትግሪኛ ደግሞ "ወጋህታ" የተሰኙ ጋዜጦች ናቸው የሚታተሙት፡፡
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር ላይም ይገኛል፡፡
አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ እንግሊዝኛና ዓረብኛ ድርጅቱ በሚያሳትማቸው ጋዜጦች የሚጠቀምባቸው ቋንቋዎች ናቸው፡፡