ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማጓጓዝና ለማሰራጨት 21 አውሮፕላኖችን ማዘጋጀቱን ገለጸ

አዲስ አበባ ህዳር 3/2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማጓጓዝና ለማሰራጨት 21 አውሮፕላኖችን ማዘጋጀቱን ገለጸ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካርጎና ሎጂስቲክ አገልግሎት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ፍጹም አባዲ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማከማቸት የሚያስችል መሰረተ ልማት ተሟልቷል።

ማጓጓዙንና ማሰራጨቱን ስኬታማ ለማድረግም አሰራር መነደፉን ጠቁመዋል።

ክትባቶቹ በባህሪያቸው ቀዝቃዛ ስፍራ የሚፈልጉ በመሆናቸው ይህንን ለማሟላት በቂ የሆነ የመሰረተ ልማት መዘጋጀቱን ጠቁመው፤ የተዘጋጁት 21 አውሮፕላኖችም የክትባቱን ደህንነት በአግባቡ የሚጠብቁ መሆናቸውን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደም የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁስ በማሰራጨት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም