በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች በቀጣዩቹ ቀናቶች ኃይል ይቋረጣል - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች በቀጣዩቹ ቀናቶች ኃይል ይቋረጣል
ህዳር 3/2013 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል በቀጣዩቹ ቀናቶች ኃይል እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለፀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ እንደሚያከናውን ነው ያስታወቀው።
በዚህም አርብ ህዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 9:00 ድረስ፣• በመነን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒያለም ቤ/ክ፣ በላዛሪስት፣ በሐምሌ 19 መናፈሻ፣ በቦሌ ሚካኤል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማህበር እና አካባቢዎቻቸው፣በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ ሀይል ይቋረጣል።
በሃና ማርያም፣ በሀይሌ ጋርመንት፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ በማንጎ ሰፈር፣ በምስራቀ ፀሃይ ገብርኤል ፊት ለፊት፣ በየተባበሩት ነዳጅ ማደያ፣ በሚካኤል ፊት ለፊት፣ በጆሞ 1 በከፊል በጆሞ 3 እና አካባቢዎቻቸውም ተጠቅሰዋል።
ቅዳሜ ህዳር 5 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ድረስ፣• በመነን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒያለም ቤ/ክ፣ በላዛሪስት፣ በሐምሌ 19 መናፈሻ እና አካባቢዎቻቸው፣በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 7:30 ድረስ ሀይል እንደሚቋረጥ ተገልጿል።
በፈረንሳይ ኤምባሲ፣ በጉራራ፣ በፊልም ማዕከል፣ በራስ ካሳ ክሊኒክ፣ በአቦ ቤ/ክ፣ በእንጦጦ ኪዳነምህረት ቤ/ክ፣ በጉርድ ሾላ፣ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ በአየር መንገድ ቤቶች እና አካባቢዎቻቸውም እንዲሁ።
እሁድ ህዳር 6 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 10:30 ድረስ፣• በፍሊንት ሰቶን ሪል እስቴት፣ በአትሌቶች መንደር እና አካባቢዎቻቸው ሀይል ይቋረጣል።
በተጨማሪም ሰኞ ህዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 9:30 ድረስ፣• በቦሌ ሚካኤል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማህበር፣ በሳሚት ኮንደሚኒየም፣ በጊዮርጊስ ቤ/ክ፣ በጃክሮስ፣ በሳሌተ ምህረት፣ በፊጋ ሆቴል እና አካባቢዎቻቸው አገልግሎቱ እንደሚቋረጥ ተጠቅሷል።
በመሆኑም ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አገልግሎቱ አሳውቋል፡፡