የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአንድ አባል ሹመት እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል - ኢዜአ አማርኛ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአንድ አባል ሹመት እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 3/2013(ኢዜአ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአንድ አባል ሹመት እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል።
በዛሬው ስብሰባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአንድ አባል ሹመትን በተመለከተ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኤክሳይዝ ታክስን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።