ቀጥታ፡

የኢፌዴሪ አየር ሃይል ጠላት ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ምርጥ ኢላማዎች ከጥቅም ውጭ አደረገ

ህዳር 2/2013 (ኢዜአ) የህወሃት ጽንፈኛ ጁንታ የአየር ሃይላችንን መቋቋም የሚያስችል ቅንጣት ያህል አቅም የለውም ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ።

የአየር ሃይሉ የጦር ጄቶች አሁንም ንጹሃን እንዳይጎዱ ጥንቃቄ በማድረግ በተመረጡ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።

የህወሃት ቡድን ‘የጦር ጄት ጥያለሁ’ ማለቱ ፍጹም ሀሰት መሆኑን አረጋግጠዋል።

የአየር ሃይል የጦር ጄቶች የጽንፈኛውን ቡድን የጦር መሳሪያ ማከማቻዎች ማውደሙን ገልጸው፤ “ቡድኑ ከአየር ሃይል አቅም በላይ የሆነ ምንም ዓይነት መሳሪያ የለውም” ብለዋል።

“ጽንፈኛ ቡድኑ በየዕለቱ የሚያሰራጨው የሃሰት መረጃም ቡድኑ በውሸት ተፈጥሮ በውሸት የኖረና ከነውሸቱ የሚቀበር መሆኑን ያሳያል” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም