የህወሃት ቡድን በርካታ ነዋሪዎችን አፍኖ በመውሰድ ሰውሯቸዋል -- የዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች - ኢዜአ አማርኛ
የህወሃት ቡድን በርካታ ነዋሪዎችን አፍኖ በመውሰድ ሰውሯቸዋል -- የዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች
የህወሃት ቡድን በርካታ ነዋሪዎችን አፍኖ በመውሰድ እንደሰወራቸውና እስካሁንም ያሉበት እንደማይታወቅ የዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
የዳንሻ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ከጽንፈኛው የህወሓት ቡድን ነፃ መውጣቷን አስመልክቶ ደስታቸውን እየገለጹ ነው።
የከተማዋ ጤና ተቋማት፣ ሱቆች፣ ሆቴሎች፣ የትራንስፖርትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተከፍተው ነዋሪዎች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ገብተዋል።
ነዋሪዎቹ የህወሃት ፅንፈኛ ቡድን በአገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ የክህደት ጥቃት ከማድረሱ በፊት ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ይደርስባቸው እንደነበርም ይናገራሉ።
በሰርግና በለቅሶ ላይ በአለባበሳቸው ጭምር በህወሃት ካድሬዎችና የፀጥታ ኃይሎች ይጠየቁ እንደነበር በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።
ዜጎች መብታቸውን ሲጠይቁ የሚታሰሩበት፣ የሚገረፉበት እንዲሁም የሚገደሉበት ሁኔታ እንደነበርም ነዋሪዎቹ ያስታውሳሉ።
ቡድኑ እስካሁን ድረስ ሕዝቡን በቅኝ ግዛት ይዞ በማቆየቱ ለውጥና ሰላም እንዳይመጣ ሲሰራ እንደነበርም ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት መንግሥት በጽንፈኛው የህወሃት ታጣቂ ኃይል ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉ ይገልጻሉ።
በቀጣይ መከላከያ ሰራዊቱን ለማጠናከር ድጋፍ እናደርጋለንም ብለዋል።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጽንፈኛ ቡድን እስኪደመሰስ ድረስ የአገር መከላከያ ሰራዊት እንዲደግፍ ጠይቀዋል።