ቀጥታ፡

ኢትዮጵያን በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች ዝግጅት ማድረግ መጀመራቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ ህዳር 2/2013 (ኢዜአ) ኢትዮጵያን በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች ዝግጅት ማድረግ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ገለጸ። 

ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት መራዘሙ ይታወቃል።

የቶኪዮ ኦሊምፒክ በአንድ ዓመት ተራዝሞ በያዝነው ዓመት ክረምት ወር ላይ "ቶኪዮ 2020" የሚለውን ስያሜ እንደያዘ ይካሄዳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ኢትዮጵያን የሚወክለው ቡድን ውጤታማ እንዲሆን ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶ ዝግጅት እንዲያደርግ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ቡድኑ ስምንት ወር ቀድሞ ዝግጅት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ገልጿል።


በዚህ መሰረትም ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ ከምትሳተፍባቸው ስፖርቶች መካከል አንዱ በሆነው የወርልድ ቴኳንዶ የሚሳተፉ ስፖርተኞች በተያዘላቸው ሆቴል በማረፍ ልምምድ መጀመራቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላትም የኮቪድ-19 ምርምራ በማድረግ አብዛኞቹ አትሌቶች ወደ ተዘጋጀላቸው ሆቴል መግባታቸው ተነግሯል።

በቀጣይ በሌሎች ስፖርት አይነቶች ተካፋይ የሚሆኑ ስፖርተኞች ወደ ሆቴል በመግባት ልምምዳቸውን የሚሰሩ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም