የአገር መከላከያ ሰራዊት የሕወሓትን የጥፋት ቡድን የውጊያ አቅም እያዳከመው ነው - ሌተናል ጀነራል ባጫ - ኢዜአ አማርኛ
የአገር መከላከያ ሰራዊት የሕወሓትን የጥፋት ቡድን የውጊያ አቅም እያዳከመው ነው - ሌተናል ጀነራል ባጫ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1/2013 (ኢዜአ) የአገር መከላከያ ሰራዊት የሕወሓትን የጥፋት ቡድን የውጊያ አቅም እያዳከመው መሆኑን በከባቢው ሰሞኑን ቅኝት ያደረጉት ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ።
ሌተናል ጀነራል ባጫ የአገር መከላከያ ሰራዊት በሰሜን ኢትዮጵያ በፅንፈኛው የህወሃት ጁንታ ላይ እየፈጸመ ስላለው ተልእኮና ግዳጅ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት በአየርና ምድር እየወሰደ ባለው እርምጃ የጥፋት ቡድኑ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን ገልጸዋል።
የጁንታው ታጣቂ ሃይል ከዳንሻ ካምፕ ስድስት ታንኮችን ለመውሰድ ሞክሮ አምስቱን የአገር መከላከያ ሰራዊት ሲቆጣጠራቸው አንዱ ደግሞ ተመትቶበት ተቃጥሏል ብለዋል።
በዚህ መሰረት የጠላት ቡድኑ ታንክ ታጠቀ ማለት የማያስችልና አንድም ቦታ በታንክ አልተዋጋም ብለዋል።
ቡድኑ የተወሰኑ መድፎች በእጁ ቢገኙም ይህን ጥቅም ላይ ሊያውል የሚችል ቡድን እንደሌለው ነው የገለጹት።
ፅንፈኛ ቡድኑ ተዋጊ ጀትም ሆነ ስቴሽን መምታት የሚያስችል አቅም የለውም ነው ያሉት ሌተናል ጀነራል ባጫ።
በቡድኑ እጅ ላይ ገብቶ የነበረ ረጅም ርቀት የሚሄድ ሚሳኤል እንዲወድም ተደርጓልም ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የጠላት ቡድኑ እንደፈለገ እንዳይንቀሳቀስ ለማድረግ ከ20 እስከ 30 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ማከማቻ በአየር ሃይላችን ወድሟል ነው ያሉት።
ሌተናል ጀነራሉ አክለውም ጠላት ለአንድ ደቂቃ እንኳን ቢሆን አየር ላይ መብረር እንደማይችል አብራርተዋል።