ቀጥታ፡

በቁጥጥር ስር የዋሉ የህወሃት ታጣቂዎች ልዩ ኃይሉና ወጣቱ የጥፋት ቡድኑ እኩይ ዓላማ ማስፈጸሚያ ከመሆን እንዲቆጠቡ አስገነዘቡ

ሁመራ፤ ህዳር 1/2013(ኢዜአ) “ልዩ ኃይሉና ወጣቱ የጥፋት ቡድኑ እኩይ ዓላማ ማስፈጸሚያ መሆን የለባቸውም” ሲሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ የ"ጽንፈኛው ህወሓት ቡድን ታጣቂዎች" ገለጹ።

ከአንድ ሳምንት በፊት በትግራይ ክልል በነበረው የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ በህወሃት ቡድን የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የአገር መከላከያ ሠራዊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተሰጠው አገርን የማዳን ተልዕኮ ሕግ ለማስከበር የኦፕሬሽን ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

የሠራዊቱ 5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የ "ጽንፈኛው ህወሓት ቡድን ታጣቂዎችን" በቁጥጥር ስር አውሏል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ታጣቂዎች የትግራይ ልዩ ኃይልን የተቀላቀሉት ኑሯቸውን አሸንፈው ለማደግ እንጂ ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጋር ለመዋጋት አለመሆኑን ገልጸዋል።

ኑሮን ለማሸነፍ በሚል ወደ ልዩ ኃይሉ ቢገቡም የህወሓት የጥፋት ቡድን እኩይ ዓላማ ማስፈጸሚያ ከመሆን ውጪ ያገኙት ነገር አለመኖሩን ነው የተናገሩት።

ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጋር መጋጨት ማለት ከኢትዮጵያ ጋር መጋጨት መሆኑንም እነዚህ በቁጥጥር ስር የዋሉ የጽንፈኛው ህወሓት ቡድን ታጣቂዎች ገልጸዋል።

የትግራይ ልዩ ኃይል እና ወጣትም የህወሓት የጥፋት ቡድን ሰላባ እንዳይሆኑ ከአገር መከላከያ ሠራዊቱ ጎን መቆም እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በአገር መከላከያ ሠራዊቱ የደረሰባቸው ምንም አይነት ችግር እንደሌለና በአሁኑ ወቅት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

የአገር መከላከያ ሠራዊት እያከናወነ ባለው የኦፕሬሽን ሥራ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛል።

1041042 Comments9 SharesLikeCommentShare

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም