ቀጥታ፡

አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ

ባህርዳር፣ ጥቅምት 29/13 (ኢዜአ) አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ።

የኣማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለሌላ ሃገራዊ ተልዕኮ በመፈለጋቸው ያቀረቡትን መልቀቂያ የከልሉ ምክር ቤት ተቀብሎ አጽድቋል።

አቶ ተመስገን ክልሉን በመሩበት ወቅት ውጤታማ ስራዎችን ማከናወናቸው የተገለጸ ሲሆን አሁን ላይ ለላቀ ሃገራዊ ሀላፊነት በመፈለጋቸው የርዕሰ መስተዳደርነታቸውን መልቀቃቸው በምክር ቤቱ ቀርቧል።

በምትካቸውም ምክር ቤቱ ክልሉን በርዕሰ መስተዳደርነት እንዲመሩ በእጩነት የቀረቡትን  የአቶ አገኘሁ ተሻገርን ሹመት አጽድቋል።

አቶ አገኘሁ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ሃላፊ በመሆን ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም