የመቀሌ፣ ሽሬ፣ አክሱም አና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሲቨል አቪዬሽን ባለስልጣን ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የመቀሌ፣ ሽሬ፣ አክሱም አና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሲቨል አቪዬሽን ባለስልጣን ገለጸ
ጥቅምት 27/2013(ኢዜአ) ከዛሬ ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሠዓት ጀምሮ የመቀሌ፣ ሽሬ ፣አክሱም እና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሲቨል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለሥልጣኑ በማህበራዊ ገጹ እንዳስታወቀው በተመሳሳይ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት (ኤርሜንስ) በተገቢው የመገናኛ ዘዴ በ(ኖታም) አንዲያውቁት ተደርጓል።