ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ አባላትን ሹመት አፀደቀ

አዲስ አበባ ጥቅምት 26/2013 (ኢዜአ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ አባላትን ሹመት በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በዛሬው ውሎውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ አባላትን ሹመት በ6 ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው ቀደም ብሎ የተመለከተውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ላይ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አጠቃላይ ሁኔታ በሚመለከትም የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለምክር ቤት አባላት ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራ ሲሆን አግባብነት ካላቸው አካላት የተወጣጡ አባላትን ያካተተ ግብረ ኃይል መቋቋሙ ይተወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም