ቀጥታ፡

ህወሃት በትግራይ ክልል በሚገኙ የኢትዮጵያ የአገር መከላከያ ሰራዊት ካምፖች ላይ ጥቃት ማድረሱ አሳስቦናል ... ማይክ ፖምፒዮ

ጥቅምት 26/2013(ኢዜአ) “ህወሃት በትግራይ ክልል በሚገኙ የኢትዮጵያ የአገር መከላከያ ሰራዊት ካምፖች ላይ ጥቃት አድርሷል የሚለው ሪፖርት አሳስቦናል” ሲሉ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

ሰላምን ለመመለስና ውጥረቶችን ለማርገብ አፋጣኝ ጥረት መደረግ እንዳለበትም ጠይቀዋል።

ከትናንት በስቲያ ሌሊት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን መግለጻቸው ይታወቃል።

ህወሐት ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ ማድረጉንና በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት መክፈቱንም መግለጻቸው ይታወሳል።

መከላከያ ሰራዊቱም በሰፈረባቸዉ ካምፖች የተከፈተበትን የከሃዲዎች ጥቃት በብቃት መክቶ ወደ ጸረ ማጥቃት እርምጃ መሸጋገሩን ትናንት ማምሻውን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም