የመከላከያ ሰራዊትን መተናኮስ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሊታገሱት የማይችሉት እኩይ ተግባር ነው- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት - ኢዜአ አማርኛ
የመከላከያ ሰራዊትን መተናኮስ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሊታገሱት የማይችሉት እኩይ ተግባር ነው- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25/2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ከማስከበር አልፎ በተለያዩ መስኮች ህዝብን በመደገፍ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊት መተናኮስ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሊታገሱት የማይችሉት እኩይ ተግባር ነው ሲል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጸ።
ምክር ቤቱ በመግለጫው እንዳለው "የአገራችንን ሉአላዊነት ከማስከበር አልፎ ህዝባችን ድጋፍ በፈለገበት መስክ ሁሉ በመሰማራት የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊታችንን መተናኮስ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሊታገሱት የማይችሉት እኩይ ተግባር ነው"፡፡
በመሆኑም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ጐን በመቆም የአገራችንን ሉአላዊነትና አንድነት የምናስጠብቅበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ብሏል፡፡
ስለሆነም ከመከላከያ ሰራዊታችን ጐን በመሆን ለአገራችን ዘብ እንድንቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ብሏል ምክር ቤቱ በመግለጫው።