በአማራ ክልል በሶሮቃና ቅርቃር አካባቢ ትህነግ ያደረገው የጦርነት ሙከራ በልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ ከሽፏል--ርዕሰ መስተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
በአማራ ክልል በሶሮቃና ቅርቃር አካባቢ ትህነግ ያደረገው የጦርነት ሙከራ በልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ ከሽፏል--ርዕሰ መስተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ ጥቅምት 25/2013 (ኢዜአ) የትህነግን ትንኮሳ ቀልብሶ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ሥራ መጀመሩን ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አስታወቁ
ትህነግ በትግራይ ክልል በሚገኘው የሀገር መከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ መንግሥት የማያዳግም ርምጃ በመውሰድ ላይ መሆኑን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አስታወቁ፡፡
በአማራ ክልል በሶሮቃና ቅርቃር አካባቢ ትህነግ የጦርነት ሙከራ ማድረጉንና በአማራ ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ መክሸፉንም ነው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን የገለፁት።
ይህንን ኃይል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ በሚደረገው ርምጃ ሕዝቡ ከመንግሥት ጎን ቆሞ ሊያግዝና አካባቢውን ነቅቶ ሊጠብቅ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
(አብመድ)