ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ የውሃ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ ተካሄደ

ጥቅምት 22/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ድርድር በበይነ መረብ ዛሬ ተካሂዷል።

በድርድሩም ታዛቢዎችና የአፍሪካ ህብረት የመደባቸው ባለሙያዎች መገኘታቸውን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዛሬውን ድርድር አስመልክቶ የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል።

ሶስቱ ሀገራት ሁለት ሁለት ባለሙያዎችን ከሶስቱም ሀገራት በመሰየም በድርድሩ አካሄድና በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት የሰየማቸው ባለሙያዎች ተጨማሪ ሚና ዙሪያ ውይይት በማድረግ ለውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሪፖርት እንዲያቀርቡ መግባባት ላይ መደረሱን ሚኒስቴሩ ያወጣው መግለጫ ያመለክታል።

ባለሙያዎቹ ጥቅምት 23/2013 ዓ.ም ተወያይተው የደረሱበትን ሪፖርት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ለሚካሄደው የውሃ ሚኒስትሮች ድርድር ያቀርባሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም