በዞኑ በ150 ሺህ ሄክታር ማሳ ላይ የነበረ የሰሊጥ ሰብል ተሰበሰበ

158

ሁመራ ጥቅምት 22/2013 ( ኢዜአ ) በትግራይ ምዕራባዊ ዞን በ150 ሺህ ሄክታር ማሳ ላይ የነበረ የደረሰ የሰሊጥ ሰብል መሰብሰቡን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ አሰታወቀ።

በመምሪያው የመስኖ ልማት ቡድን መሪ አቶ ብርሃነ ፍስሃ ለኢዜአ እንደገለጹት የደረሰ የሰሊጥ ሰብል በአንበጣ መንጋና ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሽ ሙሉ ለሙሉ ተሰብስቧል ።

በመኸር ወቅቱ በ541 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሰሊጥን ጨምሮ፣ ጤፍ፣ ገብስ፣ ባቄላ፣ ማሾ፣ ማሽላና ስንዴ ሰብሎች እንዲሁም ጥጥ መልማቱን ተናግረዋል ።

ከሰሊጥ በተጨማሪ ሌሎች የደረሱ ሰብሎችም እየተሰበሰቡ መሆኑን ጠቅሰዋል ።

በዞኑ በመኽር ወቅት ከለማው ሰሊጥ 810 ሺህ ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ አመላክተዋል ።

በቃፍታ ሁመራ ወረዳ የዋል ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ሙስጦፋ ሓጂ በሁለት ሄክታር ማሳ ያለሙትን ሰሊጥ በመሰብሰብ 6 ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን ተናግረዋል ።

በምርት ወቅቱ በነበረው የዝናብ መብዛት ያገኙት የምርት መጠን በግማሽ መቀነሱን አርሶ አደሩ አስታውቀዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም