ከንቲባዎች የአዲስ አበባን ታላላቅ ፕሮጀክቶች እየጎበኙ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባዎች የአዲስ አበባን ታላላቅ ፕሮጀክቶች እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21/2013 ( ኢዜአ) የኢትዮጵያ የ120 ከተሞች ከንቲባዎች የአዲስ አበባ ከተማን ታላላቅ ፕሮጀክቶች እየጎበኙ ነው ፡፡
ከንቲባዎቹ ከመስቀል አደባባይ እስከ ማዘጋጃ ቤት የሚካሄደውን የመልሶ ማልማትና የአረንጓዴ ሥፍራ ግንባታ አካል የሆነውን የመስቀል አደባባይ መልሶ ማልማት ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል፡፡
በመቀጠልም በቀጨኔ አካባቢ የሚካሄደውን እንስራ ፕሮጀክት በመጎብኘት ላይ ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በፕሮጀክቱ የተሰሩ የሸክላ ውጤቶችን ለከንቲባዎቹ በስጦታ አበርክተዋል፡፡
ከንቲባዎቹ በመቀጠልም የሸገርንና የእንጦጦ ፓርኮችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ ከተሞች ከንቲባዎች ትናንት መመስረቱ ይታወሳል፡፡ ፎረሙም ወይዘሮ አዳነችን ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧቸዋል