5 የሪልስቴት ኩባንያዎች በ"ገበታ ለሀገር" የእራት ግብዣ ላይ ለመሳተፍ በድምሩ የ25 ሚሊዮን ብር ኩፖን ገዙ

85

አዲስ አበባ ጥቅምት 20/2013 (ኢዜአ) በሪልስቴት ግንባታ ዘርፍ የተሰማሩ አምስት ኩባንያዎች በ"ገበታ ለሀገር" የእራት ገብዣ መርሃ ገብር ላይ ለመሳተፍ በድምሩ የ25 ሚሊዮን ብር ኩፖን ገዙ።

በገበታ ለሀገር የእራት ግብዣ መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ እያንዳንዳቸው የ5 ሚሊዮን ብር ኩፖን የገዙት ሃያት ሪልስቴት፣ ዮሲ ሪልስቴት፣ ይርጋለም ሪልስቴት፣ ካራቆሬ ሪልሰቴትና ፀሃይ ሪልስቴት ናቸው።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ኩባንያዎቹ ላደረጉት አስተዋፆ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሌሎችም የእነርሱን አርአያ በመከተል ለአገር ልማትና ግንባታ የድርሻቸውን አንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የገበታ ለሀገር የእራት ግብዣ መርሃ ግብር ከሁለት ሳምንት በኋላ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም