የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

54

ጥቅምት 17/2013 ( ኢዜአ) የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀው፤ የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ተፈታኞች በኦንላይን ምዝገባ ማካሄድ ጀምረዋል።

ምዝገባው በየአካባቢው ባሉ ትምህርት ቤቶች እየተከናወነ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሀረጓ ማሞ ተናግረዋል።

ተማሪዎች በየአካባቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች በመገኘት በወቅቱ ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል።

ምዝገባውም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል።

የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ዘንድሮ በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም