ቀጥታ፡

ቻይና ለኢትዮጵያ አምባሳደርነት ያጨቻቸው ዲፕሎማት የሀገሪቱን የከተሜነት ጉዞ የሚያሳልጡ ናቸው

አዲስ አበባ ጥቅምት 16/2013 (ኢዜአ) ቻይና ለኢትዮጵያ አምባሳደርነት ያጨቻቸው ዲፕሎማት የሀገሪቱን የከተሜነት ጉዞ የሚያሳልጡ መሆናቸውን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ቻይና ባለፈው ሳምንት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ ው ፔንግ አማካኝነት የቀድሞውን የዶንግያንግ ከተማ ከንቲባ ዛሆ ዚዩዋን ለኢትዮጵያ አምባሳደርነት አጭታቸዋለች፡፡

አዲሱ አምባሳደር “ለቦታው ከሚገባው በላይ ብቁ'' ናቸው በማለት የቀድሞ ሥራቸውን አጣቅሰው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

“የዛሆ ሹመት የቻይና መንግሥት ለቻይና-ኢትዮጵያ  ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የሚያሳይ ነው፡፡አምባሳደሩ ይህንኑ ግንኙነት በእርግጠኝነት ከፍ ወዳለ ደረጃ ያሸጋግሩታል “ በማለት ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ክፍል ፕሮፌሰርና የቀድሞ ዲፕሎማት ዴቪድ ሺን እንደተናገሩት "ሹመቱ ብቃትን ታሳቢ በማድረግ በግለሰባዊ እይታ የተከናወነ ነው ፡፡"

“የዚህ ዓይነት ሹመት በአሜሪካ የተለመደ ቢሆንም፤ በቻይና ግን አዲስ ነው” በማለት በኢትዮጵያና ቡርኪና ፋሶ በአምባሳደርነት ያገለገሉት ዴቪድ ሺን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሮድ ኤንድ ቤልት ኢኒሼቲቭን በተመለከተ የቻይና ቁልፍ አጋር ስትሆን፣ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መሥመር ነው ተብሏል፡፡

የቻይና ባለሃብቶች በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በማፍሰስ በቀላል ኢንዱስትሪ ላይ ተሰማርተዋል፡፡

በዚህ በመታገዝ ኢትዮጵያም የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ኢንዱስትሪዎችን በማቋቋም ምርቶቿን ወደ አሜሪካና አውሮፓ አገሮት በመላክ እየተጠቀመች ነው፡፡

ከለንደን ዩኒቨርሲቲ የኦሪየንታል ትምህርት ክፍል የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ፕሮፌሰር ስቴፈን ቻን የዛሆ ሹመት የሚያሳየው ቤጂንግ የኢትዮጵያ ከተሞችን ለማሳደግ ያላትን ፍላጎት ነው፣ በዚህም የቻይና ኩባንያዎች ተሳትፎ የላቀ ሚና አለው” ብለዋል፡፡

“የቀድሞው ከንቲባ የኢትዮጵያ መንግስትን የከተሜነት ስትራቴጂ በሚገባ ይገነዘባሉ"በማለት ፕሮፌሰር ቻን ተናግረዋል፡፡

“ቤጂንግ በዝግታ ግን በተጠና መንገድ አዲሱን ትውልድ በአፍሪካ ከፍ ወዳለ የዲፕሎማትነት ደረጃ እያመጣች ነው” ብለዋል፡፡

አምባሳደሮቹ በኬንያ፣ናይጄሪያ፣ሞዛምቢክና ደቡብ አፍሪካ እንደሚመደቡ አስታውቀዋል፡፡

ዲፕሎማቶቹ ወጣቶት ቢሆኑም፤ ልምድ እንዳካበቱ  ይናገራሉ፡፡

“የአሜሪካ መንግሥት አሁን ላይ አፍሪካን በተመለከተ ያሉት ኤክስፐርቶች ዕውቀታቸው የተገደበና ዘገምተኛ አካሄድ የሚከተሉ መሆናቸውን ቻይና ታውቃለች፡፡ በዚህም ቻይና ጠንካራ የአመራርና የጥናት ብቃት በመላበስ በአፍሪካ መንቀሳቀስ ትፈልጋለች” ብለዋል፡፡

ቻይና በአፍሪካ ጠንካራ የሆነ ይሁንታ ለማግኘት ተግባሯን አጠናክራ ገፍታበታለች ይላሉ ሚስተር ሺን፡፡

“ቻይና በአፍሪካ ያላትን ተፅዕኖ በተመለከተ የትራምፕ አስተዳደር ለሚከተለው ፖሊሲ ምላሽ እየሰጠች ነው ፡፡ '' ው ፔንግ ደግሞ የጥረቱ ዋና አንቀሳቃሽ ናቸው፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ሰው በእርሳቸው ቦታ ቢቀመጥ የሚያደርገው ተመሳሳይ ነገር ነው” ብለዋል አሜሪካዊው አንጋፋ ዲፕሎማት፡፡

ቻይና በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ወጣትና አዳዲስ ዲፕሎማቶችን በአምባሳደርነት እየመደበች መሆኗን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም