የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት ተመረቀ

አምቦ፣ ጥቅምት 15/2013 (ኢዜአ) በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ የተገነባ የአርቲስቱ ሀውልት ዛሬ ተመረቀ ።
በሃውልቱ ምርቃት ስነ ስርአት ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ጓደኞችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል ።
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታደሰ ቀነአ በወቅቱ እንደገለጹት ሃውልቱ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ለማስታወስ ተገንብቷል።
"ለህዝብ ነጻነት ያደረገውን ተጋድሎም ያስታውሰናል" ብለዋል።
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽት አዲስ አበባ ገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ በሰዎች ግድያ እንደተፈፀመበት ይታወሳል።