ቀጥታ፡

''በምንምና በማንም ካሰብነው መንገድ አንቀርም፤ያቀድነውን ከማሳካት የሚያግደን ምድራዊ ኃይል የለም" ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት

 አዲስ አበባ ጥቅምት 14/2013 (ኢዜአ) ''በምንምና በማንም ካሰብነው መንገድ አንቀርም፤ያቀድነውን ከማሳካት የሚያግደን ምድራዊ ኃይል የለም-ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስመልክተው ከሱዳን እና እስራኤል መሪዎች ጋር ትናንት ባደረጉት የስልክ ውይይት ግብፅ ግድቡን ልታፈርሰው እንደምትችል ሀገራቸው አሜሪካ ደግሞ ትሰጥ የነበረውን እርዳታ ማቋረጡን ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ ቤት ፕሬዝዳንቱ የህዳሴ ግድቡን አስመልክተው የተናገሩትን ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ሀሳብ ማራመዳቸውን ተከትሎ መግለጫ አውጥቷል።

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸውን ለማክበር እንጂ ጠላቶቻቸውን ለመታዘዝ ተንበርክከው አያውቁም።

ዛሬም ወደፊትም አናደርገውም።ክንዳችንን እናበርታ።ትከሻችንን እናስፋ።ልባችንንም እናጽና። ከውጭና ከውስጥ የተሠነዘረብንን ጥቃት ድል አድርገን መሻገር ብርቃችን እንዳልሆነ እናስመስክር።

በምንምና በማንም ካሰብነው መንገድ አንቀርም። ያቀድነውን ከማሳካት የሚያግደን ምድራዊ ኃይል የለም። አንድ ሆነን የምንይዘው ጋሻ ኃያላኑን ሁሉ ሲመክት የኖረ ነው።

ዛሬም ያንን ጋሻ በአንድነት እናንሣ። ሁላችንም፣ በየቦታችን፣ 24 ሰዓት፣ ለኢትዮጵያ እንቁም።ማንም ገዝቶን አያውቅም፤ወደፊትም ማንም አይገዛንም፤ታሪክ የሠሩ እጆች ዛሬም አሉ።


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም