የልዩ ዘመቻዎች ኃይል የኮማንዶ ምርቃት በብላቴ የጦር ማሰልጠኛ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14/2013(ኢዜአ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማዘዣ በአምስት ሻለቃ ያሰለጠናቸውን የኮማንዶ አባላት በብላቴ የጦር ማሰልጠኛ ማዕከል እያስመረቀ ነው።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የመከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፓሊስ ከፍተኛ አመራሮች ታድመዋል።

ወደ ልዩ ተልዕኮ የሚገቡት ተመራቂዎቹ የ33ኛ ዙር መሠረታዊ ኮማንዶና የ10ኛ ዙር የልዩ ኃይል ፀረ-ሽብር ኮማንዶ ስልጠና ነው የወሰዱት።

የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ሹማ አብደታ ምሩቃኑ የተፈጥሮም ይሁን ሰው ሰራሽ ችግሮችን ለመመከት ዝግጁነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ሜጀር ጄኔራሉ በንግግራቸው በአገሪቷ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በተለይም ደግሞ በሕዳሴ ግድብ ላይ ሊቃጡ የሚችሉ ጥቃቶችን "ለመመከት ዝግጁ መሆናችንን እገልፃለሁ ብለዋል"።  

ምሩቃኑ ወቅታዊውን አገራዊ ሁኔታ በመረዳት ለሕዝቡ የጋራ ዓላማ እንዲቆሙም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኮማንዶ አባላቱ የተለያዩ ወታደራዊ ስልቶችና የተኩስ ትርዒት አሳይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም